ሬንሜታል የተሰኘው ኩባንያ ታንኮችን ጨምሮ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን በማምረት ይታወቃል
ኩባንያው ቅርንጫፉን በዩክሬን ለመክፈት መወሰኑን በቅርቡ አሳውቋል
ሩሲያ የጀርመን ቁጥር አንድ የጦር መሳሪያ አምራች ኩባንያ ሀላፊን ለመግደል መሞከሯ ተገለጸ።
ሬንሜታል የተሰኘው የጀርመን ጦር ሙሳሪያ አምራች ኩባንያ በዓለማችን ካሉ ግዙፍ ኩባንያዎች መካከል አንዱ ነው።
ዩክሬን የሩሲያን ግስጋሴ ለማስቆም በውጊያ ላይ እየተጠቀመቻቸው ካሉ የጦር መሳሪያዎች መካከል ሊዮፓርድ የተሰኘው ታንክ ጀርመን ሰራሽ ነው።
ኩባንያው ለበርካታ የአለማችን ሀገራት የጦር መሳሪያዎችን በመሸጥ የሚታወቅ ሲሆን ለዩክሬንም እየተለገሱ ካሉ የጦር መሳሪያዎች መካከል ከፍተኛው ድርሻ የሚይዙት የዚህ ኩባንያ ምርቶች ናቸው።
እንደ ሲኤንኤን ዘገባ ሩሲያ የዚህን ኩባንያ ስራ አስኪያጅ አርሚን ፓፐርገርን ለመግደል ያደረገችው ጥረት ከሽፋል ተብሏል።
የጀርመን እና አሜሪካ የስለላ ተቋማት እና ባለሙያዎች ባደረጉት ጥረት ስራ አስኪያጁን ከመገደል አትርፈውታል ተብሏል።
ሬንሜታል ኩባንያ በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ “ሁሌም ቢሆን የደህንነት ጉዳይ ዋነኛ ትኩረታችን ነው” ብሏል።
የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አናሊና ባርቦክ በበኩላቸው ሩሲያ የተቀናጀ ጥቃት መክፈቷን ተናግረው በተለይም በመሰረተ ልማቶችን ላይ የበይነ መረብ ጥቃትን ጨምሮ ሌሎች ጉዳቶችን ለማድረስ እየሰራች ነው ብለዋል።
ሬንሜታል ኩባንያ ከአንድ ዓመት በፊት ቅርንጫፉን በዩክሬን በመክፈት በውጊያ ላይ የተበላሹ ታንኮችን እና ሌሎች መሳሪያዎችን እንደሚጠግን እና እንደሚያመርት አስታውቆ ነበር።
የሩሲያ ደህንነት ምክር ቤት ምክትል ሀላፊ ድሚትሪ ሜድሜዴቭ በወቅቱ ሬንሜታል በዩክሬን ቅርንጫፉን ከከፈተ ጥቃት እንደሚደርስበት አስጠንቅቀው ነበር።
Al-Ain
More Stories
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከፑቲን ጋር የሚያደርጉት ንግግር እየተመቻቸ መሆኑን ገለጹ።
የአሜሪካ ኮንግረስ በአለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ድምጽ ሰጠ
አስደንጋጩ የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት አልበረደም