ከሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር በቤንዚን፣ በኬሮሲን፣ በነጭ ናፍጣ፣ በቀላል ጥቁር ናፍጣ እና በከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደርጓል።
በዓለም ገበያ ላይ እየታየ ያለውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መሠረት በማድረግ መጠነኛ የመሸጫ ዋጋ ማስተካከያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
በዚህም መሠረት ከሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ሥራ ላይ የሚውለው የነዳጅ ውጤቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ እንደሚከተለው ይሆናል፡-
ቤንዚን …………………………… ብር 82.60 በሊትር
ነጭ ናፍጣ……………………… ብር 83.74 በሊትር
ኬሮሲን ……………………………. ብር 83.74 በሊትር
የአውሮፕላን ነዳጅ ………………… ብር 70.83 በሊትር
ቀላል ጥቁር ናፍጣ………………… ብር 65.48 በሊትር
ከባድ ጥቁር ናፍጣ…………………. ብር 64.22 በሊትር መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡
FBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።