በ2030 ዓ.ም የንፁህ መጠጥ ውሃን ሙሉ በሙሉ ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር “በተግዳሮቶች ፊት መፅናት” በሚል መሪ ሃሳብ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ተደራሽነት ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገ የባለ ብዙ ባለድርሻ ምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።
በዚሁ ወቅት ሚኒስትሩ እንዳመለከቱት፤ በ2030 ዓ.ም የንፁህ መጠጥ ውሃ በገጠርና በከተማ ሙሉ በሙሉ ተደራሽ ለማድረግ ታቅዷል።
ይህንን ዕቅድ እውን ለማድረግም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የንፁህ ውሃ አቅርቦትን ማሳደግ ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየመከረ ባለው በዚህ የባለ ብዙ ባለድርሻ መድረክ የፌደራልና ክልሎች መንግስታት፣ የልማት አጋሮች፣ የሲቪል ማህበራትና የሙያ ማህበራት ተገኝተዋል።
FBC
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።