የ2016 ዓ.ም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መሰጠት ጀምሯል።
በዛሬው ዕለት የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች ፈተናቸውን እየወሰዱ መሆኑ ታውቋል፡፡
ፈተናውን በይፋ ያስጀመሩት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)÷ ዛሬ የሚሰጠው ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የበይነ መረብና የወረቀት ፈተና በድብልቅ ነው ብለዋል።
በመላ ሀገሪቱ የተጀመረው የበይነ መረብና የወረቀት ፈተና እንደ ሀገር የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የተያዘው እቅድ አካል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በመላው ሀገሪቱም ፈተናው በሰላም እየተሰጠ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ይሰጣል።
የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ከ700 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች በወረቀትና በኦላይን እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል፡፡
በትግራይ ክልል ደግሞ በሁለት ዙር ፈተናው የሚሰጥ ሲሆን ከትናንት ሐምሌ 2 ጀምሮ እስከ ሐምሌ 12 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።
ይህም የሆነው በቀድሞው ሥርዓተ-ትምህርት የተማሩ በ2013 እና በ2014 የትምህርት ዘመን መፈተን የነበረባቸው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተና የሚወስዱ በመሆኑ ነው።
FBC
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።