የዘመኑ ስልጣኔ ካቀለላቸው በርካታ ነገሮች አንዱ ፎቶ ማንሳትና ቪዲዮ መቅረፅ ነው።
የማንኛውንም ሰው ምስል ማግኘትም ሆነ በአንድ ጠቅታ በማህበራዊ ድረ ገፆችና በሌሎች መገናኛ ብዙኃን ማሰራጨቱም ፎቶ የማንሳቱን ወይም ቪዲዮ የመቅረፁን ያህል ቀላል ሆኗል።
የሚዲያው ዓይነት መስፋቱና ወደ ታዳሚዎች የሚደርስበት ሁኔታ እየበዛ መሄዱ፣ በተለይም በማኅበራዊ ሚዲያዎች አማካይነት በቢሊዮኖች የሚቆጠር የዓለማችን ሕዝብ መልዕክትና መረጃ በቀላሉ መለዋወጥ የሚቻልበት ሥርዓት መፈጠሩ የሰዎችን ፎቶግራፍና ምስል በስፋት መለጠፍና ማሳየት እንዲጨምር አድርጎታል፡፡
ጋዜጣው፣ መጽሔቱ፣ ቴሌቪዥኑ፣ ፌስቡክና ዩቲዩቡ፣ ፊልምና የሙዚቃ ሥራዎች ጭምር ሥርዓት በሌለው መልኩ የሰዎችን ምስል ለሕዝብ በማሳየት የግላዊ ነፃነትን (ግላዊነትን) የሚጻረሩ ድርጊቶች አፋጻጸም ሕጋዊ እስኪመስል ድረስ ተንሰራፍቷል፡፡
ለመሆኑ በሃገሪቱ ህግ መሰረት ግለሰቦች በፎቷቸው ወይም በቪዲዮቻቸው ላይ ያላቸው መብት ከህግ አንጻር እንዴት ይታያል? የግለሰቦች ፎቶግራፍ ወይም ሥዕል የግላዊ ነጻነት ወይም መብት አካል እንደመሆኑ ግለሰቦቹ በፎቷቸው ላይ ያላቸው መብት እስከ ምን ድረስ ነው?
EBC
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።