January 24, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከሰሞኑ መሳለቂያ የሆኑበትን ቃለ መጠይቅ ያደረገችላቸው ጋዜጠኛ ከስራ ተባረረች።

በፊላዴልፊያ ግዛት የሚሰራጨው ዉርድ የተሰኘ የጥቁሮች ሬዲዮ ጣቢያ ከቃለ መጠይቁ በፊት ከጣቢያው ጋር ባደረገው ድርድር ለፕሬዝዳንት ባይደን የሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች እንዲላኩለት አድርጎ ነበር።ይሁን እንጂ ሎውፉል ሳንደርስ የተባለችው የሬዲዮ ጣቢያው ጋዜጠኛ የተሰጣትን ጥያቄዎች ከመጠየቅ ይልቅ የራሷን ጥያቄዎች ጠይቃለች ተብሏል።በዚህም ፕሬዝዳንት ባይደን “እኔ በጥቁር ፕሬዝዳንት ስር ምክትል ሆኜ ያገለገልኩ የመጀመሪያዋ ሴት ነኝ” የሚለውን ጨምሮ ራሳቸውንና ፓርቲያቸውን መሳለቂያ ያደረገ ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል።

Al-Ain