October 5, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ወጣቶች በሀገራዊ ምክክሩ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

ወጣቶች በሀገራዊ ምክክሩ ሚናቸውን እንዲወጡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያዘጋጀው የወጣቶች የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መሥፍን አርአያ (ፕ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት በዚህ ወቅት ÷ ወጣቶች የመነጋገርና የመደማመጥ ባህልን በማጎልበት በሀገራዊ ምክክሩ ሚናቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል ፡፡

ለሰላምና ለተረጋጋ የሀገረ መንግስት ግንባታ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በመድረኩ በትውልዶች መካከል መኖር ስለሚገባው ምክክር እንዲሁም በሀገራዊ ምክክሩ የወጣቶችን ሚና ማሳደግ ስለሚቻልባቸው መንገዶች የውይይት መነሻ ሃሳብ ቀርቧል።

እየተካሄደ በሚገኘው ውይይት ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ ከ200 በላይ ወጣቶች በመሳተፍ ላይ መሆናቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

FBC