ባኒያስ በተባለችው የወደብ ከተማ በተፈጸመው የሚሳኤል ጥቃት የንብረት ውድመት ደርሷል ተብሏል
እስራኤል ከ2012 ጀምሮ የኢራንን በሶሪያ መስፋፋት ይገታሉ ያለቻቸውን የአየር ጥቃቶች ስትፈጽም ቆይታለች
እስራኤል በሶሪያ የአየር ጥቃት መፈጸሟ ተነገረ።
በሜዲትራኒያን ባህር ዳርቻ በምትገኘው ባኒያስ የተሰኘች ከተማ የተፈጸመው ጥቃት መጠነኛ የንብረት ውድመት ማስከተሉን የሶሪያ ብሄራዊ የዜና ወኪል ዘግቧል።
የሶሪያ አየር ሃይል መጠናቸውን ያልጠቀሳቸውን ሚሳኤሎች መትቶ መጣሉን አስታውቋል።
ጥቃቱ ከኢራን ጋር ግንኙነት ያላቸው ሃይሎች ላይ ያነጣጠረ እንደሚሆን ተገምቷል።
የሶሪያ ዋነኛው የነዳጅ ማጣሪያ የሚገኝባት የባኒያስ ከተማ አብዛኛውን የሀገሪቱን የነዳጅ ፍላጎት ታሟላለች።
የኢራን ነዳጅ ጫኝ መርከቦችም በወደብ ከተማዋ በተደጋጋሚ የሚታዩ ሲሆን እስራኤል እነዚህ መርከቦች ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶችን በቅርብ አመታት ውስጥ ፈጽማለች።
ተንታኞች የባኒያስ ወደብ ቴህራን ወደ ደማስቆ የጦር መሳሪያ የምታስገባበት መሆኑን ይገልጻሉ።
AL-AIN
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ ንግግር ለመጀመር አጥጋቢ እቅድ እንዳልደረሳት ገለጸች