በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጅነር ነጋሽ ዋገሾ ክልሉ ከተደራጀ ወዲህ ባለፊት ዓመታት ዉስጥ የገቢ አሰባሰብ ህደትን የሚያሳልጡ ዘመናዊ የገቢ አሰባሰብ ስረዓትን በመዘርጋት የታክስና ግብር ተጠያቂነትን በማስፈን የገቢ ግብር ስሰበሰብ መቆየቱን ገልፀዋል። በዚህ ህደትም የገቢ አሰባሰብ መጠን መደጉን ገልፀዉ በ2017 በጀት ዓመትም 9 ቢልዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል። ወቅቱ የህዝብ ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጠበት ግዜ መሆኑን የጠቆሙት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ተለዋዋጭ አለም ዉስጥ የህዝብን ፍላጎት ማማላት የሚችል ሀብት ወይም በጀት ያስፈልጋል ብለዋል። ለዚህ ዋና ምንጭ የሆነዉ ግብርና ታክስ በአግባቡ መሰብሰብ ማስተዳደር ና መምራት ካልተቻለ አዳግ የሆኑ የህዝብ ጥያቀዎችን መመለስ አዳጋች ይሆናል ብለዋል። ዘጎች ለሚከፍሉት ግብር ወይም ታክስ ተመጣጣይ የሆነ አገለግሎት ከመንግሰት እንደምፈልጉ ጠቁመዉ ለዚህም ተመጣጣኝ የሆነ አገልግሎት መስጠትየምችል አቅም መፍጠር እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል። የገቢ አሰባሰብ መሰረቶችን አማጦ በመጠቀም የገቢ መሰረቶችን ማስፋት ና በአሰባሰብ ህደት ዉስጥ የህግ ተገጅነት ማስፈን እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል ። ከሰዎች ንክክ የፀዳ ዘመናዊ የሆነ የገቢ ግብርና ታክስ አሰባሰብ ስረዓት ማሳለጥ እንደሚያስፈልግ ጠቁመው ዛሬ ከኢትዮ ቴሌ ጋር በመተባበር የተጀመሩዉ ድጅታል ቴሌ ግብር የግብር ከፋዩ ጊዜና ጉልበትን በመቆጠብ አላስፈላግ የሆነ ንትርክና ማጨበርበርን የሚያስቀር ነዉ ብለዋል። ባለፊት ዓመታት በገቢ ሰክተር በተሰሩት ስራዎች ስር ነቀል ለዉጦች መመዝገባቸዉን የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ ኢንቨስትመንት መሬት አጠቃቀም ማሻሻያ፣የደረጃ’ሐ’ የግብር ትመና ፣የገጠር መሬት እርሻ መሬት መጠቀሚያ ና የእርሻ መጠቀሚያ ገቢ ማሻሻዎች ተግባራዊ መደረጋቸዉን ተናግረዋል። በ2017 በጀት ዓመትም የአከራይ ተከራይና የንብረት ክራይ እንድሁም ማዘጋጃዊ ገቢ ማሳደግ ላይ በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል። የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ በበኩላቸዉ የክልሉ መንግስት የልማት ጥያቀዎችን ለመመለስ ያስችለው ዘንድ ኢኮኖሚ ካመነጨዉ ሀብት በአግባቡ ገቢ ለመሰብሰብ ከፍተኛ ጥረት እየደረገ ይገኛል ብለዋል ።የክልሉ መንግስት የክልሉ ገቢ አቅም እንዲያድግ የተለያዩ አዋጆች ደንቦችና ሰርኩራሎችን በማዘጋጀት ና በማሻሻል የክልሉን የገቢ አሰባሰብ ለማቀላጠፍ 20ሚልዬን ብር በመመደብ ዘመናዊ የታክሰ አስተዳደር ከነበረዉ 53 በመቶ ወደ 98 በመቶ እንድደረስ ሰፊ ስራ መስራቱን ጠቁመዋል። በ2017 በጀት ዓመት በክልሉ 9ቢልዬን ብር በላይ ለመሰብሰብ መታቀዱን የጠቆሙት የቢሮ ኃላፊዋ ከሚሰበሰበው ብር 7.8 ቢልዬን ከማዘጋጃዊ ገቢ 1.1ቢልዬን ብር እንደሚሰበሰብ ተናግረዋል። በተመሳሳይ መልኩ በበጀት ዓመቱ ቀጥተኛ ካልሆኑ ታክስ 45 በመቶ እንድሁም ቀጥተኛ ያልሆኑ 45 በመቶ እንድሁም ታክስ ያልሆኑ 10በመቶ ገቢ ለመሰብሰብ ግብ መጣሉን ገልፀዋል። ክልሉ ወስጥ ካሉ 61ሺህ ግብር ከፋዮች ዉስጥ 90 በመቶ የሚሆነዉ የደረጃ ‘ሐ’ ግብር ከፋዮች በመሆናቸዉ በቀጣይ በየደረጃዉ የሚገኙ የገቢ ተቋማት ኢፍትሐዊ በሆነና በታክስ አስተዳደር በተቀመጠዉ ህግ መሰረት 45 በመቶ የሚሆኑት ን ወደ ደረጃ ‘ሀ’ለ’ ለማሸጋገር እንደሚሰራና ለዚህም የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል ። የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ኢትዮ ቴሌኮም ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አቶ ክፍሌ ካሳ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የዲጂታል ኢትዮጵያ ራዕይን ለማሳካት መጠነ ሰፊ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ከደቡብ ምዕራብ ሪጅን ኢትዮ ቴሌኮም ኦፕሬሽን ጋር ለቴሌ ብር ክፍያ የውል ስምምነት ተፈራርመዋል።ዘጋቢ ቸርነት አባተ
Woreda to World
More Stories
የቴፒ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ዝግጅት እየተገባደደ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የከተሞች ፕላን ኢኒስቲትዩት ተገለጸ፡፡
የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተመረጡ የግብርና፣ በቱሪዝም፣ በቴክኖሎጂ እና ማዕድን ዘርፎች እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበየቻይናዋ ግዛት ከፍተኛ ልዑካን የተሳተፉበት የቻይና-አፍሪካ (ኢትዮጵያ) የኢኮኖሚ እና የንግድ ትብብር ጉባኤ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝም ና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር በዓለም ለ45ኛ በኢትዮጵያ ለ37ኛ በክልሉ ደረጃ ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረዉ የዓለም የቱሪዝም ቀን ”ቱሪዝም ለሰላም” በሚል መር ቃል በቦንጋ ከተማ እየተከበረ ነዉ።