የአራት ኪሎ-ቀበና-ኬንያ ኤምባሲ ኮሪደር ሥራ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር ገለጹ፡፡
አካባቢውን አረንጓዴ የማድረግ ጥረቱ በጉልህ እንደሚታይም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው የገለጹት፡፡
ባለፉት ሳምንታት የምሽቱን ውበት እንዳደነቅነው ዛሬ ደግሞ የማለዳን እይታ በኮሪደር ልማታችን ተመልክተናል ብለዋል።
ለስኬቱ በሥራው ለተሳተፉት የከተማው አስተዳደር እና በሙሉ ፈቃድ ለተሳተፉ የግሉ ሴክተር ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የከተማችንን የመኪና ማቆሚያ እጥረት የሚቀርፉ የፓርኪንግ ቦታዎች ተገንብተዋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ የእግር ጉዞን የሚያበረታቱ የእግረኛ መንገዶች ተስፋፍተው መሠራታቸውን አመላክተዋል፡፡
ይህን ባሕል መንከባከብ እና ማሳደግ እንደሚገባ አስገንዝበው÷ ሁላችንም ህልው ለሆነው አዲስ መልክ ጠባቂዎች መሆን አለብን ሲሉ ገልጸዋል
FBC
More Stories
የዓድዋ ድል መታሰቢያ አዲስ አበባን የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ
የጋራ ጥረቶቻችን ረሃብን በማጥፋት ለሁሉም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ርብርብ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚያስችሉ ተስፋ አለኝ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)