። ከክልሉ 6ቱ ዞኖች ከ14 ሺህ 8 መቶ በላይ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን ወደ ተመደቡበት በክልሉ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የማጓጓዝ ተግባር መከናወኑን ቢሮዉ ለሬድዮ ለጣቢያችን ገልጿል።የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊና የመማር ማሰተማርና ምዘና ዘርፍ ሀላፊ ዶክተር ደስታ ገነመ ለጣቢያችን እንደገለጹት ዘንድሮ ላይ ከክልሉ የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች የተሻለ ዉጤት እንዲያስመዘግቡ ከተለያዩ ባለድርሻዎች ጋር አስፈላጊዉን ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል።በተለይ በፈተናዉ ወቅት የተከለከሉና የሚፈቀዱ ጉዳዮችን በሚመለከት በየደረጃዉ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ ስከናወን መቆየቱን የጠቆሙት ዶክተር ደስታ ገነመ በዛሬዉ ዕለትም በክልሉ በሚገኙ ዩኒበርሲቲዎች 14 ሺህ 8 መቶ 47 የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎችን ለመጀመሪያዉ ዙር ፈተና የማጓጓዝ ተግባር በሰላማዊና በተሳካ ሁኔታ መከናወን ተናግረዋል።ከመጭዉ ዓርብ ዕለት ጀምሮ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞችን የመመለስና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችን ደግሞ ለ2ኛዉ ዙር ፈተና የማጓጓዝ ስራ ስለሚከናወን የትራንስፖርቱ ዘርፍ ማህበራት በዛሬዉ ዕለት በሰሩት ልክ በወቅቱ ተገኝተዉ እንዲያከናዉኑ አሳስበዋል።የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ግቢ ሥራ አስፈጻሚ መንግስቱ ከተማ በበኩላቸዉ ግቢዉ የምግብ ፣ የመኝታና የህክምና አገልግሎትን ጨምሮ ተማሪዎች የሚያስፈልጋቸዉን ግብዓቶች በበቂ ሁኔታ መዘጋጀቱንና ተገቢዉ ፍተሻና ጥበቃ ተደርጎላቸዉ 1 ሺህ 54 የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ወደ ግቢዉ መግባታቸዉን ጠቁመዋል።የሸካ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ መስፍን ዓለሙ ተማሪዎች በሚገባ በራስ መተማመን ፈተናዉን እንዲሠሩ ለማደረግ በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን አስታዉሰዉ ከዞኑ 1 ሺህ 7 መቶ 20 የማህበራዊ ተማሪዎችን ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለፈተና የማጓጓዝ ስራ በሰላም መጠናቁንም አክለዋል። ዘጋቢ ጌትነት ገረመዉ
Woreda to World
More Stories
የዓድዋ ድል መታሰቢያ አዲስ አበባን የኮንፈረንስ ማዕከል በማድረግ አይነተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ
የጋራ ጥረቶቻችን ረሃብን በማጥፋት ለሁሉም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ርብርብ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚያስችሉ ተስፋ አለኝ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)