ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ኢትዮጵያና ዑጋንዳ በቀጣናው ሰላምና ፀጥታን በማስፈን ረገድ ጉልህ ሚና አላቸው አሉOn Jul 3, 2024 73አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ዑጋንዳ ካላቸው ጠንካራ ስትራቴጂክ ግንኙነት በተጨማሪ በቀጣናው ሰላምና ፀጥታን በማስፈን ረገድ ጉልህ ሚና እንዳላቸው የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አስገነዘቡ፡፡ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ከዑጋንዳ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር ተወያይተዋል፡፡በውይይታቸውም ኢትዮጵያ እና ዑጋንዳ ካላቸው ጠንካራ ስትራቴጂክ ግንኙነት በተጨማሪ በቀጣናው ሰላምና ፀጥታን በማስፈን ረገድ ጉልህ ሚና እንዳላቸው ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ አስረድተዋል፡፡ሁለቱ ሀገራት በመከላከያ ዘርፍ የሚያደርጉት ትብብርም ፋይዳው የጎላ ስለመሆኑ ማስገንዘባቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ በበኩላቸው ዑጋንዳና ኢትዮጵያ ዘመናትን የተሻገረ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን አውስተዋል፡፡ሀገራቱ በመከላከያ ዘርፍ እንዲሁም በቀጣናው ሰላም በማስፈን ረገድ ያላቸውን የጋራ ሚናና ትብብር በማስቀጠል ቀጣናው ብሎም አፍሪካ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚገባቸውም አመላክተዋል፡፡
FBC
More Stories
የዩክሬን አየር ሃይል 106 የሩሲያ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡
ትራምፕ ጦርነቱን በመጀመር እና ስምምነት ላይ ባለመድረስ ዩክሬንን ወቀሱ
የማሻ ወረዳ ምክር ቤት 4 ኛ ዙር12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን12 ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።