January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ለምክር ቤቱ ማብራሪያ ይሰጣሉ

ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ለምክር ቤቱ ማብራሪያ ይሰጣሉOn Jul 4, 2024  69አዲስ አበባ፣ ሰኔ 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ፡፡6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ይካሄዳል፡፡በኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 55 (17) እና በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 81 (3) እና አንቀፅ 92 መሰረት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደበኛ ስብሰባው በመገኘት በፌዴራል መንግስቱ የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ፡፡በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 55 (11) እና በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 76 መሰረትም ምክር ቤቱ የ2017 የፌዴራል መንግስት በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን አስመልክቶ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ አዳምጦ ረቂቅ በጀቱን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡በምክር ቤቱ 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የሚጀመረውን ስብሰባ ሒደት በሁሉም አማራጮች በቀጥታ የሚያስተላልፍ ይሆናል፡፡

FBC