November 22, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በኮምቦልቻ ከተማ ተጀመረ

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በዛሬው ዕለት በኮምቦልቻ ከተማ ተጀምሯል።

በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

አቶ አረጋ በዚህ ወቅት÷ በክረምት በጎ ፈቃድ ችግኝ በመትከል፣ ደካሞችን በመርዳት፣ ማዕድ በማጋራት፣ አካባቢን በማፅዳት ለሁለተናዊ እድገት መስራት ያስፈልጋል፤”በመረዳዳት ፣ በመተጋዝ ህብረተሰቡን ማገልገልም ይገባል” ብለዋል።

የክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ እርዚቅ ኢሳ በበኩላቸው ÷ከ8 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሚሰማሩ ፈቃደኞች መኖራቸውን ጠቁመው፤ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በዚህም ለአቅመ ደካሞች አዲስ ቤት መስራትና መጠገን፣ ደም መለገስ፣ ችግኝ መትከል፣ ጽዳትና ውበት ፣ አርሶ አደሮችን ማገዝና ሌሎችም እንደሚከናወን መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትም ወጣቶች፣ ባለሃብቶችና ሌሎች ህብረተሰቡን በገንዘብ፣ በጉልበትና በቁሳቁስ ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት አስተዋጽኦ በማበርከት የመንግስትን የልማት ክፍተት ለመሙላት ያግዛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አስቻለው ብርሃኑ÷ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ከ48 ሺህ በላይ ሰዎችን በማሳተፍ በተለያዩ የልማት ሥራዎች ከ55 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ስራ ለማከናወን መታቀዱን ተናግረዋል።

FBC

You may have missed