January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የሀውቲ ታጣቂዎች በእስራኤሏ ሀይፋ ወሳኝ ኢላማ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ገለጹ

በኢራን እንደሚደገፉ የሚነገርላቸው የሀውቲ ታጣቂዎች በመርከቦች ላይ የመጀመሪያውን ጥቃት የሰነዘሩት ባለፈው ህዳር ወር ነበር

የሀውቲ ታጣቂዎች በትናንትናው እለት በኢራቅ ከሚንቀሳቀሰው እስላማዊ ታጣቂ ጋር በመሆን በእስራኤሏ ሀይፋ የሚገኝን ወሳኝ ኢላማ መምታታቸውን ገልጸዋል

የሀውቲ ታጣቂዎች በእስራኤሏ ሀይፋ ወሳኝ ኢላማ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ገለጹ።

የሀውቲ ታጣቂዎች በትናንትናው እለት በኢራቅ ከሚንቀሳቀሰው እስላማዊ ታጣቂ ጋር በመሆን በእስራኤሏ ሀይፋ የሚገኝን ወሳኝ ኢላማ መምታታቸውን ገልጸዋል።

የሀውቲ ቃል አቀባይ ያህያ ሳርኣ በቴሌቪዥን ባለስተላለፈው መልእክት ወታደራዊ ኦፐሬሽኑ የተካሄደው “በበርካታ ባለክንፍ ሚሳይሎች” ነው ብሏል። ቃል አቀባዩ የተመታው ኢላማ ምን እንደሆነ አልገለጸም።

የሀውቲ ታጣቂ ቡድኖች ከእስራኤል ጋር እየተዋጋ ላለው የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ሀማስ አጋርነት ለማሳየት ከባለፈው ህዳር ጀምሮ በመርከብ መስመሮች ላይ የድሮን እና የሚሳይል ጥቃት እያደረሱ ይገኛሉ።

በኢራን እንደሚደገፉ የሚነገርላቸው የሀውቲ ታጣቂዎች በመርከቦች ላይ የመጀመሪያውን  ጥቃት የሰነዘሩት ባለፈው ህዳር ወር ነበር።

ታጣቂዎቹ እስካሁን በሰነዘሯቸው በርካታ ደርዘን በሚቆጠሩ ጥቃቶች ሁለት መርቦች ያሰጠሙ ሲሆን ሌላ አንድ ደግሞ በቁጥጥራቸው ስር አውለዋል። በእነዚህ ጥቃቶች ሶስት የመርከብ ሰራተኞችም ገድለዋል።

አሜሪካ እና እንግሊዝ በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረሰላጤ በመርኮቦች የሚያደርሰውን ጥቃት ለመከላከል በሀውቲዎች ላይ ዘመቻ ከከፈቱ ቆይተዋል።

ሀገራቱ የመን ውስጥ በሚገኙት የሀውቲ ይዞታዎች ላይ ጥቃት እያደረሱ መሆናቸውን ገልጸዋል። ሆኖም ግን ይህ እርምጃ ታጣቃዎቹ በመርከቦች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት ማስቆም አልቻለም።

የሀውቲ ታጣቂዎች እስራኤል በጋዛ የምታደርሰውን ዘመቻ ካላቆመች እና በቂ የሰብአዊ እርዳታ የማይገባ ከሆነ፣ በቀይ ባህር በሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን እንደሚቀጥሉ መግለጻቸው ይታወሳል።

Al-Ain