የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዛሬው ዕለት ወደ ፖላንድ ሪፐብሊክ ርዕሰ መዲና ዋርሶ አዲስ በረራ ጀመሩን አስታውቋል።አዲሱ በረራ በሳምንት አራት ቀናት እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን፤ በአፍሪካ እና በፖላንድ መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሻግር እንደሚሆን ከአየር መንገዱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ትልቁ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ እንደሆነም ይነገርለታል።
EBC
More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ