July 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በፈረንሳይ የፓርላማ ምርጫ ስደተኛ ጠል ፓርቲዎች አብላጫውን ድምጽ አሸነፉ።

በአክራሪ ቀኝ ዘመም የፖለቲካ ቅኝታቸው የሚታወቁት ዣን ማሪ ለፔን የሚመራው ናሽናል ራሊ ፓርቲ በፈረንሳይ የታችኛው ምክር ቤት ውስጥ አብላጫውን ሊይዝ እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል።በምርጫው ቀኝ ዘመም ፓርቲው ከምክር ቤቱ አጠቃላይ ወንበር 33.2 በመቶ ያሸነፈ ሲሆን፤ ግራ ዘመሙ ጥምር ፓርቲ 28.1 በመቶ ድምጽ ሲያገኝ ለዘብተኛው የማክሮን ስብስብ ደግሞ 21 በመቶ ድምጽ ማግኘቱ ታውቋል።ይህም ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ማብቃት በኋላ ቀኝ ዘመም ፓርቲዎች የምክርቤቱን አብላጫ ድምጽ ለመያዝ ሲቃረቡ በታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ ያደርገዋል።

Al-Ain