January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ በጋምቤላ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር አከናወኑ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ “የምትተክል ሀገር፣ የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ ሃሳብ የጀመርነውን የዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በጋምቤላ ክልል አስቀጥለናል ብለዋል፡፡መርሐ ግብሩን ዛሬ በጋምቤላ ክልል በአኙዋሃ ዞን በዲማ ወረዳ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ማከናወናቸውንም ገልጸዋል፡፡ከዚህ ቀደም በዚህ መርሐ ግብር ዓለምን ያስደመመ ስኬት አስመዝግበናል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ለዚህ ድል ደግሞ መንግስት እና ህብረተሰቡ በጋራ ያደረጉት ርብርብና ቁርጠኝነት ወሳኝ ነበር ነው ያሉት፡፡የአረንጓዴ ልማት በህብረተሰቡ ዘንድ ባህል ሆኖ እንዲቀጥል እና ለሌሎች ስራዎች እንደማስፈንጠሪያነት ያገለግል ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካል ሚናውን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Al-Ain