January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የፌዴሬሽን ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 3ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን በምክር ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ እያካሄደ ይገኛል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ለጉባኤው የተያዙ አጀንዳዎችን ያቀረቡ ሲሆን፤ ምክር ቤቱም የቀረቡትን አጀንዳዎች መርምሮ በሙሉ ድምጽ በማፅደቅ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡ ምክር ቤቱ በመደበኛ ጉባኤው ላይ የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርትን ጨምሮ ለጉባኤው የተያዙ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

EBC