July 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የምክር ቤት አባላት በአዲስ አበባ የተጠናቀቁ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ጎበኙ

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በአዲስ አበባ የተጠናቀቁ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። ጉብኝቱ በምክር ቤቱ የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጂጌ (ዶ/ር) የተመራ ሲሆን፤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለምክር ቤቱ አባላት ገለፃ በማድረግ አስጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ከፒያሳ አራት ኪሎ እና ከሜክሲኮ ሣር ቤት የተጠናቀቁ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች ምልከታ ተደርጎባቸዋል። የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ ፕሮጀክቱ የአፍሪካ መዲና የሆነችውን አዲስ አበባ እንደስሟ አዲስና ልዩ ከተማ እንድትሆን አድርጓታል ብለዋል።

EBC