July 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

እስራኤል አስራቸው የነበሩትን 55 ፍልስጤማውያን ለቀቀች

እስራኤል በጋዛ እያካሄደችው ያለው መጠነሰፊ ጥቃት አሁንም ቀጥሏልእስራኤል አስራቸው የነበሩትን 55 ፍልስጤማውያን ለቀቀች።እስራኤል የሆስፒታል ዳይሬክተርን ጨምሮ ከጋዛ ወስዳ አስራቸው የነበሩትን 55 ፍልስጤማውያን መልቀቋን የፍልስጤም የጤና ባለስልጣን ተናገሩ።ከተለቀቁት ውስጥ አቡ ሰልሚያ አንዱ ነው። የእስራኤል ወታደሮች አቡን በቁጥጥር ስር ያዋሉት ባለፈው ህዳር ወር አል ሽፋ ሆስፒታልን በወረሩበት ወቅት ነበር።አቡ ከተለቀቀ በኋላ በፍለስጤም ሚዲያዎች ባስተላለፈው የቪዲዮ መልእክት፣ የእስራኤል ባለስልጣናት በፍልስጤማውያን እስራኖች ላይ “በየቁኑ አካላዊ ጥቃት እና ማዋረድ” ያደርሳሉ ሲል ይከሳል። የእስራኤል ባለስልጣናት ይህን ክስ አይቀበሉትም።እስራኤል ሀማስ እና ሌሎች ታጣቂ ቡድኖች በሆስፒታሉ ተጠልለው ለወታደራዊ አላማ እያዋሉት ነው የሚል ክስ ታቀርባለች።የፍልስጤም የጤና ባለስልጣናት የእስራኤል ወረራ በርካታ ሆስፒታሎች እንዲዘጉ እና አገልግሎታቸውን በእጅጉ እንዲቀንሱ በማድረግ ንጹሃንን ለአደጋ አጋልጠዋል ይላል።በአለምአቀፍ ህግ መሰረት ሆስፒታሎች ያላቸውን ከለላ የሚያጡት ለወታደራዊ አላማ ከዋሉ ብቻ ነው።የእስራኤል ጦር በድንበር አካባቢ ባሉ ማህበረሰቦች ላይ 20 ሮኬቶችን በዛሬው እለት መተኮሳቸውን ገልጸዋል። በጥቃቱ ጉዳት ስለመድረሱ አልታወቀም።እስራኤል በፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ ላይ ወታደራዊ ዘመቻ የከፈተችው፣ ሀማስ ባለፈው ጥቅምት ወር የእስራኤልን ድንበር ጥሶ በመግባት 1200 ሰዎችን ከገደለ እና 250 የሚሆኑን ደግሞ አግቶ ከወሰደ በኋላ ነው።እስራኤል ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እየወሰደች ባለው መጠነሰፊ የአየር እና የእግረኛ ጦር ጥቃት የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 37 መድረሱን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።ሀማስን ጨርሶ ለመደምሰስ እቅድ የያዘችው እስራኤል አሁን ላይ የመጨረሻ ምሽጉ ይገኝበታል ያለቻትን በደቡብ ጋዛ ድንበር የምትገኘው ራፋ ከተማ እያጠቃች ነው። 

Al-Ain