January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ስፔን ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች

በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ መርሐ ግብር ስፔን ጅርጂያን 4 ለ 1 በመርታት ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀለች። ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ በምድብ ሁለት ዘጠኝ ነጥብ በመያዝ በአንደኛ ደረጃ ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለችው ስፔን በአውሮፓ ዋንጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈችውንና ከምድብ ስድስት በ4 ነጥብ ምርጥ ሶስተኛ ሆና ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለችውን ጆርጂያን አሸንፋለች። ስፔን በሩብ ፍጻሜው ከአዘጋጇ ጀርመን ጋር ትጫወታለች። በጥሎ ማለፉ በተደረጉ ጨዋታዎች ስዊዘርላንድ፣ ጀርመን፣ እንግሊዝ እና ስፔን እስካሁን ሩብ ፍጻሜውን የተቀላቀሉ ሀገራት ሆነዋል።