July 2, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ስዊስ ዲያግኖስቲክስ ኢትዮጵያን ጎበኙ

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ስዊስ ዲያግኖስቲክስ ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል፡፡ የህክምና ማዕከሉ አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተጀመረውን ራዕይ ለማሳካት እንደሚያግዝ ከንቲባዋ ገልጸዋል፡፡ የማዕከሉ አገልግሎት እንዲስፋፋ እና ሌሎች የግል ባለሃብቶች በጤናው ዘርፍ ይበልጥ እንዲሰማሩ የከተማ አስተዳደሩ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል፡፡ መሰል የጤና ማዕከላት መበራከት ከሃገር ወጥተው መታከም የማይችሉ ወገኖች የተሻለ ህክምና እንዲያገኙ ከማስቻሉም ባሻገር የውጪ ምንዛሬን እንደሚያስቀር ከንቲባዋ በማኀበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

EBC