January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በሀሰተኛ ባለአንድ መቶ ብር ግብይት በመፈፀም ላይ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎችን ከያዙት ሀሰተኛ ገንዘብ ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የቦንጋ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ

፡፡ የቦንጋ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር መለሰ ጌታቸው እንደገለፁት የከተማው ፖሊስ የወንጀል መረጃ ኢንተለጀንስ ባለሙያዎች ባደረጉት ክትትል በቦንጋ ከተማ 02 ቀበሌ ልዩ ስሙ ባንድራ ተብሎ በሚጠራበት ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት በቦንጋ ከተማ በሚውለው የቅዳሜ ገበያ ላይ ሁለት ተጠርጣሪዎች ከአርሶ አደሩ በግ በመግዛት ሀሰተኛ ባለ አንድ መቶ የብር ገንዘብ እንደሰጡት ከሀሰተኛ ብሩ ጋር በቁጥጥር መዋላቸውን አስረድተዋል፡፡ፖሊስ ተጠራጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር አውሎ በተደረገ ፍተሻ ሀሰተኛ ባለ አንድ መቶ በፍሬ 103 ወይንም አስር ሺህ ሶስት መቶ እንደተገኘባቸው የገለፁት ፖሊስ አዛዡ ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ ምርመራ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡ህብረተሰቡ ግብይት በሚያከናውንበት ወቅት አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ያሳሰቡት ዋና ኢንስፔክተር መለሰ በግብይት ወቅት አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲመለከት አቅራቢያው ለሚገኙ የፀጥታ መዋቅር ጥቆማ እንዲሰጥ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡በመጨረሻም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት እና ኮሚንኬሽን በክልሉ ካፋ ዞን፤ቤንች ሸኮ ዞን እና ሸካ ዞን ባለሁለት መቶ ሀሰተኛ የገንዘብ ዝውውር መኖሩን እንዲሁም ሀሰተኛ ገንዘብ ሲያባዙ የነበሩ በቤንች ሸኮ ዞንና በሸካ ዞን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፆ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የጥንቃቄ መልዕክቶችን ሲያስተላልፍ ቆይቷል፡፡

#የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት