December 3, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ወታደራዊ ትብብር ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ገለጸች

 ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የቆየ ወታደራዊ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት የውጭ ጉዳይና መከላከያ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ሴናተር ስቴፋኒያ ክራክሲ ገለጹ።

የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ (ኢ/ር) እና ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በጣሊያን ምክር ቤት በሴናተር ስቴፋኒያ ክራክሲ የተመራ የልዑካን ቡድን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም ሴናተሯ ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የቆየ ወታደራዊ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ፍላጎት ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ለቀጠናው ሀገራት ወሳኝ ሚና ያላት መሆኗን አንስተው፤ ሀገራቸው በሁለንተናዊ መልኩ ከኢትዮጵያ ጋር አጋርነቷን ማጠናከር እንደምትፈልግ መግለጻቸውን የመከላከያ ሚኒስትር ጽህፈት ቤትን ዋቢ አድርጎ የመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ አመልክቷል።

አይሻ መሐመድ (ኢ/ር) በበኩላቸው በኢትዮጵያና በጣሊያን መካካል ያለውን የቆየ ወታደራዊ ትብብር ከፍ ወዳለና ወደላቀ ደረጃ ለማሳደግ ጣሊያን ላሳየችው ፍላጎት አመስግነዋል።

ኢትዮጵያ ከጣሊያን ጋር ያላትን ወዳጅነት ለማጠናከር ከፍተኛ ፍላጎት ያላት መሆኗንም አረጋግጠዋል።

FBC