የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ከኬንያ መንገድ እና ትራንስፖርት ካቢኔ ፀሃፊ ኪፕቹምባ ሞርኮሜን ጋር በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ በናይሮቢ ተወያይተዋል።በውይይታቸውም የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ጉዳዮች ላይ የተወያዩ ሲሆን፤ በተለይም ሁለቱን ሀገራት በመሰረተ ልማት ማስተሳሰር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።በተጨማሪም በኢትዮጵያ እና በኬንያ መካከል የጋራ የንግድ እና የኢኮኖሚ ዕድገት ትብብርን ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር ማድረጋቸው ተገልጿል።በውይይቱ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ መሳተፋቸውን ከትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
EBC
More Stories
“አስቸኳይ ፓስፖርት እናሰራላችኋለን” በሚል ሰዎችን ሲያጭበረብሩ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
3ኛው የፓርላማ ዜጎች ፎረም እየተካሄደ ነው
ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ እንዲጠናከር ጥሪ ቀረበ