January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን የፖሊስ መኮንኖችና እጩ መኮንኖች እያስመረቀ ነው

በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፕሬዚዳንት ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር እና የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፣ አምባሳደሮች እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ በአራት የማስተርስ ድግሪ ፕሮግራሞች እጩዎችን ያስመረቀ ሲሆን፤ በሥነ-ወንጀል እና የወንጀል ፍትህ፣ በሰላም እና የህዝብ ደህንነት ጥናት፣ በአስተዳደር እና የለውጥ አመራር፣ በደህንነት ዘርፍ አስተዳደር እና በሌሎች የትምህርት መስኮች ከ400 በላይ የፖሊስ መኮንኖች እና እጩ መኮንኖችን እያስመረቀ ነው።

EBC