የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ በጣሊያን ሴኔት የውጭ ጉዳይና መከላከያ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ሴናተር ስቴፋኒያ ክራክሲ የተመራ የጣሊያን የፓርላማ ልዑክን ተቀብለው አነጋግረዋል።በውይይታቸውም፤ የሁለትዮሽ፣ አህጉራዊ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ መክረዋል።በአፍሪካ ቀንድ ዙሪያ ያሉ የተለያዩ የልማት እና የጸጥታ ችግሮችን በተመለከተም ሁለቱ ወገኖች ተወያይተዋል።የጣሊያን መንግስት ኢትዮጵያን በተለያዩ ዘርፎች ለመደገፍ የሚያደርገውን ትብብር አምባሳደር ታዬ አድንቀዋል።በሀገራቱ መካከል ያለው ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ሁለቱ ወገኖች ጠቁመዋል።አምባሳደር ታዬ ከሰብዓዊ ዕርዳታ በተጨማሪ በቀጠናው በልማት ፕሮጀክቶች ላይ በትብብር መስራት ለበርካታ ዜጎች ህይወት መሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው አንስተዋል።በተጨማሪም ቀጠናዊ የጸጥታ ችግሮችን ከመቅረፍ አኳያ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብር እና መግባባት አስፈላጊነት ላይ ምክክር መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።
FBC
More Stories
የቴፒ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን ዝግጅት እየተገባደደ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የከተሞች ፕላን ኢኒስቲትዩት ተገለጸ፡፡
የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተመረጡ የግብርና፣ በቱሪዝም፣ በቴክኖሎጂ እና ማዕድን ዘርፎች እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበየቻይናዋ ግዛት ከፍተኛ ልዑካን የተሳተፉበት የቻይና-አፍሪካ (ኢትዮጵያ) የኢኮኖሚ እና የንግድ ትብብር ጉባኤ በአዲስ አበባ ተጀምሯል።
የፌደራል ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል ቱሪዝም ና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር በዓለም ለ45ኛ በኢትዮጵያ ለ37ኛ በክልሉ ደረጃ ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረዉ የዓለም የቱሪዝም ቀን ”ቱሪዝም ለሰላም” በሚል መር ቃል በቦንጋ ከተማ እየተከበረ ነዉ።