January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ክርክር ትራምፕ በባይደን ላይ የበላይነትን ተቀዳጅተዋል ተባለ።

ጆ ባይደን ድምጻቸው ደክሞ፣ በራስ መተማመናቸው ጠፍቶ፣ አቀርቅረው፣ ሃሳባቸው ተበትኖና አንደበታቸው ተሳስሮ ነበር ክርክሩን የጨረሱት።በክርክሩ ባይደን የትራምፕን የወንጀል ክሶች እና የ2020ውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለመቀልበስ ያደረጓቸውን ሙከራዎች በማንሳት ሞግተዋል።የቀድሞው ፕሬዝዳንት በበኩላቸው ባይደንን በኢኮኖሚ፣ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እና በክርክሩ ባሳዩት ድክመት ሲተቿቸው አምሽተዋል።ለ90 ደቂቃዎች ከተካሄደው ክርክር በኋላ ከህዝብ የተሰበሰበ አስተያየት ትራምፕ 67 በመቶ ድምጽ በማግኘት ክርክሩን በሰፊ ልዩነት ማሸነፋቸውን አሳይቷል።

Al-Ain