June 30, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

100 ሺህ ዶላር የሚያሸልመው አዲሱ የፊፋ የእግር ኳስ ውድድር ምንድን ነው?

አርሰን ቪንገር አምባሳደር የሆኑበት ይህ ውድድር የፊታችን ነሃሴ ለሶስት ቀናት ይካሄዳልበውድድሩ ላይ አሰልጣኞች እና ተጫዋቾ ባሉበት ሆነው ይፋለሙበታል ተብሏል100 ሺህ ዶላር የሚያሸልመው አዲሱ የፊፋ የእግር ኳስ ውድድር ምንድን ነው?የዓለም እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፊፋ ከዚህ በፊት ተደርጎ የማይታወቅ ለየት ያለ ውድድር ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡የቀድሞው የአርሰናል እግር ኳስ ቡድን አሰልጣኝ የሆኑት አርሰን ቪንገር አምባሳደር የሆኑበት ይህ ውድድር የእግር ኳስ ጠበብቶች ባሉበት ሆነው በታክቲክ የሚፋለሙበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡በውድድሩ ለይ በመላው ዓለም ያሉ አሰልጣኞች ወደ ፊፋ ድረገጽ በመግባት መመዝገብ በውድድሩ ለይ ለመሳተፍ የመጀመሪያው መስፈርት ነውም ተብሏል፡፡ውድድሩ ከነሀሴ 23 እስከ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳል የተባለ ሲሆን በፊፋ ኢስፖርት ስር መዘጋጀቱን ቪንገር ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡እንደ ዘገባው ከሆነ እግር ኳስ ተጫዋቾችም በፊፋ ድረገጽ ላይ ተመዝግበው በውድድሩ ላይ መካፈል ይችላሉ የተባለ ሲሆን አሰልጣኞች ከዚህ በፊት ያልሞከሯቸውን ታክቲኮች በበይነ መረብ አማካኝነት በጌም መልክ እንዲተገብሩት ያስችላቸዋልም ተብሏል፡፡

Al-Ain