June 30, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ያሉንን እምቅ ጸጋዎች በማልማት ከተረጂነት አስተሳሰብ መላቀቅ እንደሚንችል አሁን የታዩ ያሉ ስኬቶች ማሳያዎች ናቸው አቶ አበበ ማሞ”

ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ፤ለተሟላ ሀገራዊ ሉአላዊነትና ክብር”በሚል መርህ የብልጽግና ፓርቲ ሸካ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮችና ፈፃሚዎች ጋር በቴፒ ከተማ ውይይት አካሂዷል ።በውይይቱ ላይ የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ እንደገለፁት ያሉንን እምቅ ጸጋዎች በማልማት ከተረጂነት አስተሳሰብ መላቀቅ እንደሚንችል አሁን የታዩ ያሉ ስኬቶች ማሳያዎች ናቸው ብለዋል። ሀገራችን ያሏትን ጸጋዎች በሚፈለገው መልኩ ባለማልማቷ ለዘመናት ከተረጂነት መውጣት እንዳልቻለችና ተረጂነት አንገት የሚያስደፋ መሆኑ ሁሉም ዜጋ በተሰማራበት መስክ ተረጂነትን በመጠየፍ ምርታማነትን ለማረጋገጥ መስራት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል። ተረጂነትን ሙሉ ለሙሉ ማስቀረት እንደሚቻል ባለፉት ዓመታት በሁሉም የልማት ሥራዎች የተመዘገቡ ውጤቶች ማሳያ በመሆናቸው ይህንን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።ለአብነትም በግብርናው ዘርፍ በበጋ መስኖ ስንዴ፣ በሌማት ትሩፋትና በኢንዱስትሪ ዘርፎች እየተመዘገቡ ያሉ ስኬቶችን ጠቅሰዋል። ለውይይቱ የመነሻ ጽሑፍ ያቀረቡት የሸካ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ፓለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዘሪሁን አንደሞ ከተረጂነት አስተሳሰብ ለመላቀቅ በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል። የብልጽግና ጉዞ ማሳካት የሚቻለው ከልመናና ከተረጂነት የተላቀቀ፣ ነብሰ ወከብ ገቢው ያደገ ማህበረሰብ ሲፈጠር በመሆኑ ለዚህ ሲኬት በጋራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።መግባባት፣ መዘጋጀትና በተቀናጀ መንገድ የልማት ሥራን ማፋጠን ክብረ-ነክ የሆነውን ተረጂነትን ማስወገድ እንደሚያስችልም ጠቁመዋል።በማህበረሰቡ ውስጥ የቆየውን የእርስ በእርስ የመረዳዳት የመተሳሰብ ልምድ በማስቀጠል ስናመርት ከራስ ተርፎ ለሌላው ለመትረፍ ማሰብ ያስፈልጋል ብለዋል።የአካባቢውን ፀጋ በመጠቀም የሚገጥሙንን አደጋዎች መቋቋም የሚችል ማህበረሰብ በመፍጠር ማምረት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሰራት እንደሚስፈልግም አንስተዋል ።የውይይቱ ተሳታፊ አመራሮች እንደ ሀገር ከተረጂነት አስተሳሰብ ለመውጣት መግባባት ላይ መድረስ እንደሚገባ ጠቁመው፤ ለዚህም እንደ ሀገር እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችን በሁሉም ደረጃ በማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።በበጋ የመስኖ ስንዴ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በእንሰት ፣በአረንጓዴ አሻራና በሌሎችም ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶች ከተረጂነት አስተሳሰብ ለመላቀቅ ትልቅ ጉልበት መሆናቸውንም ጠቅሰው ይህንን በሁሉም አካባቢዎች ማስፋት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል። ዞኑ ካለው እምቅ የተፈጥሮ ጸጋ፣ ማምረት ከምንችለው መሬትና ካለን የአረሶአደር ጉልበት ተጠቅመን የተሻለ ውጤታማ ለመሆን መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል ።እያንዳንዱ ሰው ተረጂነትን ለማስቀረት የተጀመረውን ሀገራዊ ግብ ለማሳካት የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባም ጠቁመዋል። ዘገባው የዞኑ መ/ኮ/ገጽ/ቤ/ት ነው።