”በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ ” በሚል መርህ የሸካ ዞን ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች መምሪያ የ2016 ዓ.ም የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃግብር በሸካ ዞን ጌጫ ከተማ ተካሂዷል።በውይይቱም ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ እንደገለጹት በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ቃል የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ካለፉት ጊዜያት በላቀ ደረጃ እንዲሰራ ወጣቶችና በጎ ፈቃደኞች ግንባር ቀደም ሚናቸውን እንዲወጡ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሁሉም መስኮች ትኩረት የሚሰጥ ሆኖ በተለይ ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመደገፍና የመኖሪያ ቤት በመስራት፤ የትምህርትና ስልጠና አገልገሎት በመስጠት ፤ ወባንና መሰል ተዛማጅ በሽታዎችን መከላከል መሰረት ያደረገ የጤና ዘመቻ ስራ ለመስራት ፤ በሰላምና ፀጥታ ስራዎችና በአረንጓዴ ልማት ስራዎች ጨምሮ በሌሎችም መስኮች ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል። ያለ ህብረተሰቡ ተሳትፎ የልማት ዕቅድ ማሳካት እንደማይቻልና ወጣቱ ተደራጅቶ በበጎ ተግባራት ከተሰማራ አቅም መሆን እንደሚችል ገልፀው፤ የበጎ ፍቃድ ተግባራት እንደባህል ተወስዶ ማስቀጠል እንደሚገባ አስተዳዳሪው አሳስበዋል።በውይይቱም የሸካ ዞን ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ትዕግስት ከበደ እንደገለጹት በዞኑ የበርካታ ዜጎችን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ያለው የበጎ ፈቃድ ለበርካቶች የተሻለ ግልጋሎት እየሰጠ በመሆኑ ተግባሩ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።የበጎ ፈቃድ አገልገሎት ከጀመረ በርካታ አመታትን ያስቆጠረ ብሆንም ከአላማው አንፃር ገና መሰራትን የሚጠይቅ በመሆኑ በትኩረት ማስቀጠል ይኖርብናል ብለዋል።ባለፈው ዓመት በተከናወነው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራ ዞኑ ከ 2 መቶ 80 ሺህ በላይ የሚሆኑ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራት ተከናውነል።በዚህም ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ በሚገመት ወጪ በ13 የተለያዩ ዘርፎች ሥራዎች መሠራታቸውን መሰራቱ ተገልጿል ።በተያዘው የክረምት ወራት ደግሞ ከ61 ሺህ በላይ የሚሆኑ በጎ ፈቃደኞችን ያሳተፈ 1 መቶ 73 ሺህ በላይ የሚሆኑ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስራ ለመስራት መታቀዱ አሳስበዋል።እንደ ዞን አቅመ ደካሞችን ከማስደሰት ጎን ለጎን የአረጋውያን ቤት ግንባታ ፣ የደም ልገሳን የወባ መከላከልን ጨምሮ ሁሉን አቀፍ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሥራዎችን ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።ከበጎ ተግባር ሥራዎች ጎን ለጎን የሴቶች ጥቃትን ለመከላከል በተለይም በጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በሰፊው እንደሚሰጥ ተመላክቷል።የወባ በሽታ በዞኑ በሁሉም አካባቢዎች የጤና ስጋት እየሆነ በመምጣቱ በክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራም የውይይት ተሳታፊዎች አበክረው ተናግረዋል።በመጨረሻም የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላና የአቅመ ደካማ አረጋውያን ቤት ግንባታ ማስጀመር መርሃግብር ተካሂዷል።በውይይቱ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ አመራሮችና ባለሙያዎችን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ስል የሸካ ዞን መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት ዘግቧል።
Woreda to World
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።