January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ኢትዮጵያ ለምስራቅ አፍሪካ ሰላም መረጋገጥ በሙሉ ዝግጁነት ላይ እንደምትገኝ ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ገለፁ

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሞተራይዝድ ሻለቃ አሁን ላይ ያለበትን ዝግጁነት ጎብኝተዋል። ፊልድ ማርሻሉ በጉብኝታቸው ሞተራይዝድ ሻለቃው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስታንዳርድ መሰረት ዝግጁነት ላይ እንደሚገኝ መመልከታቸውን ተናግረዋል። ሞተራይዝድ ሻለቃው በተሟላ የሰው ሀይልና ቴክኖሎጂ ቁመና ላይ እንደሚገኝ የተናገሩት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፤ ሻለቃው ለማንኛውም ተልዕኮ ዝግጁ መሆኑን ለማረጋገጥ መቻላቸውንም ገልፀዋል። ኢትዮጵያ ለአፍሪካ በተለይም ለምስራቅ አፍሪካ ሰላምና መረጋጋት ትልቅ አበርክቶ እንደነበራትም ፊልድ ማርሻሉ አስታውሰዋል።