የስደተኞችና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ከባይደን የእድሜ መግፋትና የትራምፕ የወንጀል ክስ ጥፋተኝነት ባሻገር የተፎካካሪዎቹ መከራከሪያ ይሆናሉ
ቀዳሚ ገፅዜናአስተያየትፖለቲካኢኮኖሚማህበራዊልዩልዩስፖርትየመረጃ ሳጥንተመልከትፖለቲካየባይደን እና ትራምፕ የፊት ለፊት ክርክር አጀንዳዎችየስደተኞችና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ከባይደን የእድሜ መግፋትና የትራምፕ የወንጀል ክስ ጥፋተኝነት ባሻገር የተፎካካሪዎቹ መከራከሪያ ይሆናሉአል-ዐይን 2024/6/27 13:47 GMTአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ፣ የዩክሬን እና ጋዛ ጦርነትን በተመለከተ የሚያቀርቧቸው ሀሳቦችም ቀጣዩን ተመራጭ ፕሬዝዳንት እንደሚያመላክቱ ይጠበቃልየአሜሪካ የወቅቱ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንና የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ምሽት ፊት ለፊት ይከራከራሉ።ለ1 ስአት ከ30 ደቂቃ በሚወስደው ክርክር ከግል ጉዳዮች ባሻገር ዋናዋና ሀገራዊና አለማቀፋዊ ጉዳዮች አቋማቸውን የሚያንጸባርቁበት ክርክር በአትላንታ በሚገኘው የሲኤንኤን ስቱዲዮ ይካሄዳል።በ2020ው ምርጫ ሁለት ጊዜ ያደረጉት የምርጫ ክርክር በቃላት መወራረፍ የታጀበና ስርአቱን ያልጠበቀ በመሆኑም በዛሬው እለት አንደኛው ሲያወራ የሌላኛው ማይክ የሚጠፋ ይሆናል።የስደተኞች ጉዳይ፣ ኢኮኖሚ፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እንዲሁም የዩክሬን እና የጋዛው ጦርነት የክርክሩ ዋነኛ አጀንዳዎች ይሆናሉ።ስደተኛ ጠል ንግግር በማድረግ የሚታወቁት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዴሞክራቱ ባይደን በህገወጥ ስደተኞች ዙሪያ የተለሳለሰ አቋም ይዘዋል በሚል ይወቅሷቸዋል።ዳግም ወደስልጣን ከተመለሱም በርካታ ህገወጥ ስደተኞችን ወደ መጡበት እንደሚመልሱ በምርጫ ቅስቀሳቸው ሲናገሩ ተደምጠዋል።ባይደን በበኩላቸው አሜሪካዊ ዜጋ ያገቡና ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ ለሌላቸው ሰዎች ከለላ የሚሰጥ ፖሊሲ በቅርቡ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። በዛሬው ክርክርም ይሄው ጉዳይ ዋነኛ የክርክራቸው ነጥብ እንደሚሆን ተገልጿል።ባይደን እና ትራምፕ የባንኮች ወለድ መጨመር፣ የዋጋ ንረት እና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች ላይም ይከራከራሉ፡፡
ቀዳሚ ገፅዜናአስተያየትፖለቲካኢኮኖሚማህበራዊልዩልዩስፖርትየመረጃ ሳጥንተመልከትፖለቲካየባይደን እና ትራምፕ የፊት ለፊት ክርክር አጀንዳዎችየስደተኞችና የኢኮኖሚ ጉዳዮች ከባይደን የእድሜ መግፋትና የትራምፕ የወንጀል ክስ ጥፋተኝነት ባሻገር የተፎካካሪዎቹ መከራከሪያ ይሆናሉአል-ዐይን 2024/6/27 13:47 GMTአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ፣ የዩክሬን እና ጋዛ ጦርነትን በተመለከተ የሚያቀርቧቸው ሀሳቦችም ቀጣዩን ተመራጭ ፕሬዝዳንት እንደሚያመላክቱ ይጠበቃልየአሜሪካ የወቅቱ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንና የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ ምሽት ፊት ለፊት ይከራከራሉ።ለ1 ስአት ከ30 ደቂቃ በሚወስደው ክርክር ከግል ጉዳዮች ባሻገር ዋናዋና ሀገራዊና አለማቀፋዊ ጉዳዮች አቋማቸውን የሚያንጸባርቁበት ክርክር በአትላንታ በሚገኘው የሲኤንኤን ስቱዲዮ ይካሄዳል።በ2020ው ምርጫ ሁለት ጊዜ ያደረጉት የምርጫ ክርክር በቃላት መወራረፍ የታጀበና ስርአቱን ያልጠበቀ በመሆኑም በዛሬው እለት አንደኛው ሲያወራ የሌላኛው ማይክ የሚጠፋ ይሆናል።የስደተኞች ጉዳይ፣ ኢኮኖሚ፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እንዲሁም የዩክሬን እና የጋዛው ጦርነት የክርክሩ ዋነኛ አጀንዳዎች ይሆናሉ።ስደተኛ ጠል ንግግር በማድረግ የሚታወቁት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዴሞክራቱ ባይደን በህገወጥ ስደተኞች ዙሪያ የተለሳለሰ አቋም ይዘዋል በሚል ይወቅሷቸዋል።ዳግም ወደስልጣን ከተመለሱም በርካታ ህገወጥ ስደተኞችን ወደ መጡበት እንደሚመልሱ በምርጫ ቅስቀሳቸው ሲናገሩ ተደምጠዋል።ባይደን በበኩላቸው አሜሪካዊ ዜጋ ያገቡና ህጋዊ የመኖሪያ ሰነድ ለሌላቸው ሰዎች ከለላ የሚሰጥ ፖሊሲ በቅርቡ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል። በዛሬው ክርክርም ይሄው ጉዳይ ዋነኛ የክርክራቸው ነጥብ እንደሚሆን ተገልጿል።ባይደን እና ትራምፕ የባንኮች ወለድ መጨመር፣ የዋጋ ንረት እና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲዎች ላይም ይከራከራሉ፡፡ ሚሊየኖችን ያፈናቀሉትና አሜሪካ እጇን ባስገባችባቸው የዩክሬን እና የጋዛ ጦርነት ዙሪያ የሚደረገው ክርክርም ይጠበቃል።አሜሪካ ከሩሲያ እና ቻይና ጋር ያላትን ግንኙነት በማስተካከል ዙሪያ የተለያየ አቋም ያላቸው የ2024ቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተፎካካሪዎች በምሽቱ ክርክር አቋማቸውን ያንጸባርቃሉ።የሁለቱ ተፎካካሪዎች ልዩነት ጎልቶ ይታይበታል ተብሎ የሚጠበቀው ሌላኛው ጉዳይ ታይዋንን በተመለከተ የሚያነሱት ነጥብ ነው።ባይደን ቻይና የግዛቴ አካል ናት የምትላትን ታይዋን በሃይል ለመቆጣጠር ከሞከረች ልናግዛት እንችላለን የሚል አስተያየት ሲሰጡ ተደምጠዋል።ትራምፕ በበኩላቸው ታይፒ የአሜሪካውያንን የንግድ ተቋማት እያዳከመች ነው በሚል ዋሽንግተን የምታደርገውን ድጋፍ እንድታቆም ሲቃወሙ ነበር።የግል ጉዳዮችን በተመለከተ ሁለቱ እጩዎች ይጎነታተሉባቸዋል ተብለው ከሚጠበቁ ሀሳቦች መካከል የባይደን የእድሜ ሁኔታ እና የትራምፕ የወንጀል ክስ ጥፋተኝነት ይጠበቃሉ፡፡
Al-Ain
More Stories
ሰሜን ኮሪያ በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እለት በርካታ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈችፒዮንግያንግ በጥቂቱ ሰባት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን መተኮሷን የጃፓን የመከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል
የእስራኤል-ሐማስ ጦርነት እና የደረሱ ውድመቶች በንጽጽር
እስራኤል በሀማስ ጥቃት አንደኛ አመት እለት ሊቃጣባት የሚችል ጥቃት ለመከላከል በተጠንቀቅ ላይ ነች