January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የሚኒስትሮች ም/ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

አቅጣጫ የሚያስፈልጋቸው አዳዲስ ዓለም አለምቀፋዊ፣ አህጉራዊ እና ሃገራዊ የሳይበር ደህንነትጉዳዮች በዘርፉ ውጤታማነት ላይ ተፅዕኖ የፈጠሩ በመሆኑ፤ የግል እና የመንግስት ቅንጅታዊ እና የትብብር አሰራር በግልጽ ማስቀመጥ በማስፈለጉ እና ሌሎችም ዋና ዋና የትኩረት መስኮችን ያካተተ ግልጽ የአፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ዘዴ ያለው ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ምክር ቤቱ በፖሊሲው ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡5. ብሄራዊ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ፖሊሲ ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየበት ጉዳይ ነው፡፡አርቲፊሺያል ኢንተለጀንስ (AI) በአለም ዓቀፍ ደረጃ ከተዋወቀበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ ሀገራት ከጥቃቅን የመዝናኛ እና የመገልገያ ዘዴዎች እስከ ብሔራዊ ደኅንነትና መረጃ አገልግሎት ላሉ ቁልፍ ጉዳዮች እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡ሀገራችንም ቴክኖሎጂውን በይበልጥ ለማኅበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ አገልግሎት ለማዋልና የሀገር ደህንነትን በማስጠበቅ በዘርፉ ተወዳዳሪ አቅምን ለመፍጠር ተቋም ከማቋቋም ጀምሮ በርካታ ስራዎች የተሰሩ ቢሆንም ቀሪ ስራዎችን መስራት ይጠበቅባታል። የተጀመረውን ለማስቀጠል፣ ዘርፉን ለማሳደግ፣ መንግስት በዘርፉ ሊደርስ የፈለገበትን ግብ ለማመላከት እና ዘርፉ የሚገራበትን አቅጣጫ ለማሳየት በሚረዳ መልኩ ብሄራዊ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ፖሊሲ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ምክር ቤቱ በፖሊሲው ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶች ታክለውበት ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡6. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው በጤና ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ ወቅቱ የደረሰበትን የህክምና አገልግሎቶች ታሳቢ ያደረገ፣ የጤና አገልግሎትን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል እና የጤና አገልግሎት አስተዳደር ስርዓትን የሚዘረጋ ግልጽ እና ወጥ የሆነ የሕግ ማእቀፍ በስራ ላይ ማዋል አስፈላጊ በመሆኑ ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡7. ከዚያም ምክር ቤቱ የተወያየው የመድሀኒት ፈንድ እና የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልግሎት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይነው፡፡ጥራታቸው የተረጋገጠ መሠረታዊ መድኃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋና ዘላቂነት ባለው መልኩ ለተጠቃሚው ሕብረተሰብ ማቅረብ የሚያስችል ዘመናዊ የመድኃኒት አቅርቦት ሠንሰለት ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡8.በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው የጤና ፋይናንስ ስትራቴጂ ላይ ነው፡፡ሀገራችን በአለምአቀፍ ደረጃ የፈረመችውን የዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካትና የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎትን መሠረት ያደረገ ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚያስፈልገዉን በቂ እና ቀጣይነት ያለው የሀብት አሰባሰብ እና የወጪ አሸፋፈን ስርአት መዘርጋት የሚያስችል የጤና ፋይናንስ ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቧል፡፡ምክር ቤቱ በስትራቴጂው ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

FBC