June 30, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ከሶማሌላንድ ጋር የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነት አስመልክቶ በዲጂታል ሚዲያው ላይ እየተሰራጩ ያሉ ሀሰተኛ መረጃዎችን ህብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አሳሰበ

ከሶማሌላንድ ጋር የተደረገውን የመግባቢያ ስምምነት አስመልክቶ በዲጂታል ሚዲያው ላይ እየተሰራጩ ያሉ ሀሰተኛ መረጃዎችን ህብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አሳስቧል፡፡ አካባቢያዊ፣ ክልላዊ እና ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ይፋዊ ግንኙነቶች በፅህፈት ቤቱ ይፋዊ የዲጂታል አማራጮች ብቻ እንደሚሰራጩ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታውቋል። የፅህፈት ቤቱን ሎጎ አላግባብ በመጠቀም የውሸት መረጃዎችን ከሚያሰራጩ አካላት ማህበረሰቡ እራሱን እንዲጠብቅም የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አሳስቧል፡፡

EBC