January 23, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በአውሮፓ ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ማን ከማን ይገናኛል?

17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ከሁለት ቀናት እረፍት በኋላ ቅዳሜ በጥሎ ማለፍ ውድድሮች ይመለሳል

ለዋንጫው ቅድመ ግምት የተሰጣቸው አራት ሀገራት ጥሎ ማለፉን መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋልበ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ጥሎ ማለፉን የተቀላቀሉ 16 ሀገራት ታውቀዋል፡፡በውድድሩ ለዋንጫ ቅድመ ግምት ከተሰጣቸው ሀገራት እንግሊዝ ደካማ የሚባል አፈጻጸም ቢኖራትም ጥሎ ማለፉን መቀላቀሏን አረጋግጣለች፡፡ በሁለት ጨዋታዎች አቻ ወጥታ አንድ ጨዋታ አሸንፋ ጥሎ ማለፉን የተቀላቀለችው እንግሊዝ በጥሎ ማለፉ በሚኖራት ጨዋታዎች ዝቅተኛ የማሸነፍ ግምት ተሰጥቷታል፡፡ ቅዳሜ በሚጀምረው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ሲውዘርላንድን ከጣሊያን ሲያገናኝ አዘጋጇ ሀገር ጀርመን ከዴንማርክ ጋር የምትጫወት ይሆናል፡፡

AL-AIN