June 30, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በአካባቢዉ የሚገኘዉን የፈጥሮ የቀርከሃ ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም ከተፈለገ ዘመናዊ አሰራሮችን መከተል እንደሚገባ ተገለጸ።

የቀርከሃ ውጤቶች በአሁኑ ወቅት ለገበያ ያላቸው ተቀባይነት እና የስራ ዕድል ከመፍጠር አንጻር የሚያበረክተው አስተዋጽኦ እያደገ ብመጣም በሸካ ዞን ከ28 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ የተፈጥሮ የቀርከሃ ሀብት አጠቃቀም ከተለሚዷዊ አሰራር ያልተሻገረ በመሆኑ ለዘመናት እያባከነ መቆዩቱ ይነገራል። አቶ ከበደ ገቢቶ ቀርከሃን በዘመናዊ መልክ እንዴት ማዘጋጀት እንደሚቻል በ1976 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በእደ ጥበብ ላይ ከተሰጠዉ ስልጠና ባገኙት እዉቀት በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በመንግስትና በግል ድርጅቶች ግብዣ መሠረት ልምዳቸዉን ስያካፍሉ እንደቆዩ ተናግረዋል። አሁን ላይ ኑሮአቸውን በሚዛን አማን ላይ እንዳደረጉና የተለያዩ ባለድረሻ አካላት ድጋፍ ብያደርጉ በዘመናዊ መንገድ ያላቸዉን ሙያ ለወጣቶች ለማካፈል ዝግጁ መሆናቸዉን ገልጸዋል። አቶ ይደነቁ ዳክቶ የማሻ ከተማ ስራ ክህሎት ንግድ ገበያ ልማት ኢንተርፕራይና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ ስሆኑ በአካባቢዉ የሚገኘዉን ሀብት በዘመናዊ መንገድ ማህበረሰቡን በሚጠቅም መልኩና የስራ ዕድል ለመፍጠር የሚያግዙ ሀሳቦችን ለመደገፍ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። የማሻ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ዲን አቶ አድኖ ከበደ በበኩላቸዉ ኮለጁ የቀርከሃን ምርት ዘመናዊ አሰራርን ተከትሎ የመስራት ፍላጎት ያላቸዉን ሰዎች ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ኮለጁ ስልጠና ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል ።

ዘጋቢ አማኑኤል ምትኩ