November 7, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

አሜሪካዊው ተራራ ወጪ ለ10 ቀናት በቀን 4 ሊትር ውሃ እየጠጣ ሕይወቱን አቆይቷል

በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ለእግር ጉዞ ወጥቶ ከሳምንት በላይ በተራራማ ስፍራዎች ጠፍቶ የቆየው ግለሰብ ብዙ ውሃ እየጠጣ ህይወቱን ማቆየቱ ተሰምቷል።
ሉካስ ማክሊሽ የተባለው ይህ ግለሰብ በተራራማ ስፍራ ለእግር ጉዞ (ሃይኪንግ) በወጣበት በመጥፋት ለ10 ቀናት ብቻውን አሳልፎ ቤተሰቦቹ ሲያፈላልጉት ቆይተዋል።

በወቅቱ በአካባቢው በተከሰተ ሰደድ እሳት ምክንያት በስፍራው የነበሩ አቅጣጫ ጠቋሚዎች መውደማቸው ግለሰቡ እንደ አወጣጡ እንዳይመለስ አድርጎታል።
እንደወጣ የቀረውን ቤተሰባቸውን አፋልጉን ያሉት ቤተሰቦቹም ለፖሊስ ጥቆማ ሰጥተው፥ በአነስተኛ ሰው አልባ አውሮፕላን በተደረገ ፍለጋ በህይወት መገኘቱ ተሰምቷል።

በወቅቱ ግለሰቡ በተራራማው ስፍራ የድረሱልኝ ጥሪ ያቀርብ የነበረ ቢሆንም፥ በትክክል አቅጣጫው ባለመታወቁ ምክንያት ለቀናት ብቻውን እንዲቆይ አስገድዶት እንደነበርም ነው የተገለጸው።

በተራራማው ስፍራው ቆይታው ታዲያ በሚረግጠው ጫማ ውሃ በማጠራቀም እስከ 4 ሊትር ውሃ በቀን ይጠጣ እንደነበር ተናግሯል።

በወቅቱ ሲገኝ ሰውነቱ ተጎሳቁሎና ከስቶ ቢታይም ለህይወቱ አስጊ አይደለም ተብሏል።

Ahadu Radio