በሾይጉ እና ጌራሲሞቭ ላይ የወጣው ትዕዛዝ የእስር ማዘዣ የወጣባቸውን ከፍተኛ የሩሲያ ተጠርጣሪዎቹ ቁጥር ስምንት አድርሶታል
ዩክሬንም የአይሲሲ አባል ባትሆንም አይሲሲ በግዛቷ ውስጥ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን እንዲያይ ፍቃድ ሰጥታለች
አለምአቀፉ ፍርድ ቤት በቀድሞው የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ላይ የመያዣ ትዕዛዝ አወጣ።
አለምአቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት(አይሲሲ) በቀድሞው የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌ ሾይጉ እና በኢታማዦር ሹሙ ጀነራል ቫለሪ ጌራሲሞቭ የእስር መያዣ ትዕዛዝ አውጥቷል።
በሁለቱ ጀነራሎች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ የወጣው ሩሲያ በዩክሬን እያካሄደች ባለው ወታደራዊ ዘመቻ ወቅት የጦር ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ተጠርጥረው ነው ተብሏል።
የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን የዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ከፈንጆቹ የካቲት 2022 ወዲህ ፈጽመውታል በተባለው ትልቅ ለውጥ ሰርጌ ሾይጉን ባለፈው ወር ከመከላከያ ሚኒስትርነት አንስተው የሩሲያ የጸጥታ ምክር ቤት ጸኃፊ አድርገዋቸዋል።
መቀመጫውን ዘሄግ ያደረገው ፍርድ ቤት ሰርጌ እና ጌራሲሞቭ በዩክሬን በንጹሃን እና በንጹሃን መሰረተልማቶች ላይ ጥቃቶች እንዲፈጸሙ በማዘዝ በጦር ወንጀል እና በሰብአዊነት ላይ በተፈጸመ ወንጀል መጠርጠራቸውን ገልጿል።
ዳኞች ሁለቱ ተጠርጣሪዎች የሩሲያ ጦር ከፈረንጆቹ ጥር 2022-ሚያዝያ 2023 በዩክሬን የኤሌክትሪክ መሰረተልማቶች ላይ ጥቃት አድርሰዋል ብሎ ለማመን የማያስችል መነሻ አግኝተዋል ብሏል አይሲሲ ባወጣው መግለጫ።
የአይሲሲ አባል ያልሆነችው ሩሲያ የዩክሬን የኃይል መሰረተልማት ወታደራዊ ኢላማ መሆኑን እና በንጹሃን እና በንጹሃን መሰረተልማቶች ላይ ግን ጉዳት አለማድረሷን በተደጋጋሚ ገልጻለች።
ዩክሬንም የአይሲሲ አባል ባትሆንም አይሲሲ በግዛቷ ውስጥ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን እንዲያይ ፍቃድ ሰጥታለች።
በሾይጉ እና ጌራሲሞቭ ላይ የወጣው የመያዧ ትዕዛዝ አይሲሲ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ የእስር ማዘዣ ያወጣባቸውን ከፍተኛ የሩሲያ ተጠርጣሪዎቹ ቁጥር ስምንት አድርሶታል።
ይህ ቁጥር የዩክሬን ህጻናት ወደ ሩሲያ በማሸገር በጦር ወንጀል የተጠረጠሩትን ፑቲንን ይጨምራል።
የአይሲሲ ችሎት የሚያስፈጽምበት የራሱ ፖሊስ ስሌለው ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ በአባል ሀገራት ትብብር ላይ ጥገኛ ነው።
ሩሲያ አይሲሲ የሚያወጣቸውን የእስር ማዘዣዎች በተደጋጋሚ ውድቅ ስታደርግ ቆይታለች።
Al-Ain
More Stories
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከፑቲን ጋር የሚያደርጉት ንግግር እየተመቻቸ መሆኑን ገለጹ።
የአሜሪካ ኮንግረስ በአለም አቀፉ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ድምጽ ሰጠ
አስደንጋጩ የሎስ አንጀለስ ሰደድ እሳት አልበረደም