January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከጅቡቲ አቻቸው ጋር ተወያዩ

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የተመራ ልዑክ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ጅቡቲ የገባ ሲሆን ከጅቡቲ አቻቸው ማህሙድ አሊ የሱፍ ጋር ውይይት አድርገዋል። በውይይታቸውም፤ ሁለቱ ወገኖች የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማጠናከር እና ቁልፍ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል። ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ የወደብ አገልግሎቶችን በተመለከተ ያላቸውን ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ምክክር መደረጉን በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል።

EBC