January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ7ኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ ሽልማትን አሸነፈ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኢንዱስትሪው የአቪዬሽን ኦስካር ተብሎ በሚጠራው የስካይትራክስ መድረክ ለ7ኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ ሽልማትን አሸንፏል፡፡አየር መንገዱ በተጨማሪም የአፍሪካ ምርጥ የቢዝነስ ክፍል አየር መንገድ ሽልማትን ለ6 ተከታታይ ዓመታት ማሸነፉ ተገልጿል፡፡እንዲሁም አየር መንገዱ የአፍሪካ ምርጥ የኢኮኖሚ ክፍል አየር መንገድ ሽልማትን ለ6 ተከታታይ ዓመት ማሸነፍ ነው የተጠቆመው፡፡ከዚህ ባለፈም በአፍሪካ የኢኮኖሚ ክፍል ምርጥ ምግብ አገልግሎት ሰጪ አየር መንገድ ሽልማትን ማሸነፉን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡ውጤቱን ተከትሎም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በስኬቶቹ ሁሉ አብረውት ለተጓዙ ደንበኞች ምስጋና አቅርቧል፡፡

FBC