July 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነዉ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ከሃይማኖት አባቶች እና በክልሉ ከሚገኙ ሁሉም ዞኖች ከተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች እና ተፅኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ጋር በወላይታ ሶዶ ከተማ በመወያየት ላይ ይገኛሉ፡፡ መድረኩ “የአባቶች ሚና በልዩነት ለተዋበ ጠንካራ የህዝቦች አንድነት” በሚል መሪ ቃል ነዉ እየተካሄደ የሚገኘው። ክልሉ የሰላም የመቻቻል እና የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ እየተደረገ ላለው ጥረት የሀገር ሽማግሌዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል። በውይይቱ ከርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፤ የዞን አመራሮች፤ የሃይማኖት አባቶች፤ የሀገር ሽማግለዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መገኘታቸውን ከክልሉ ኮሙዪኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

EBC