የማሻ ወረዳ ግብርናና አከባቢ ጥበቃ ጽህፈት ቤት ምክትል የተፈጥሮ ሀብትና አከባቢ ጥበቃ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መብራቴ ጨጊቶ በወረዳው ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ የችግኝ ተከላ ስራ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መረሃ ግብር የቡና ፣ የመኖ እጽዋት ፣የአቦካዶ እና የተለያዩ የደን ዝሪያዎች እንደሚተከሉ ገልጸው እነዚህ ችግኞች ኢኮኖሚያዊና ኢኮሎጅያዊ ፋይዳ ያላቸው መሆኑን ጠቁመዋል::በወረዳው የቡና ችግኝ ጨምሮ 5 ነጥብ 1ሚልዮን ለመትከል እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው 1 ነጥብ 9 ሚልዮን የቡና ችግኝና 3 ነጥብ 2 ሚልዮን የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያላቸው ችግኞች በተራቆቱ ቦታዎች የሚተከሉ መሆኑን ተናግረዋል::በዚህም 803 ሄክታር በላይ መሬት ለመሸፈን ዕቅድ መያዙን በማንሳት የተለያዩ ፕሮጀክቶች በወረዳው በችግኝ ማዘጋጀት ላይ የተሰማሩ መሆናቸውንም አብራርተዋል።ከአሁን በፊት በተለያዩ ጊዜያት የተተከሉ ችግኞች በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የገለፁት የጽ/ቤቱ ምክክትል ኃላፊ የጽድቀት መጠኑ 85 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል:: የአለም የአየር ንብረት ለውጥ በሰው ልጆች ላይ የተለያዩ አሉታዊ ጫናዎችን እያሳደረ በመሆኑ የተፈጥሮ ሚዛን ለመጠበቅ ሁሉም የየራሱን ተሳትፎና አበርክቶ ልያደርግ እንደሚገባም ተናግረዋል ።
ዘጋቢ ልጃለም ማሞ
More Stories
የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ አዲስ አበባ ገቡ
የጋራ ጥረቶቻችን ረሃብን በማጥፋት ለሁሉም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ርብርብ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚያስችሉ ተስፋ አለኝ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ሰሜን ኮሪያ በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እለት በርካታ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈችፒዮንግያንግ በጥቂቱ ሰባት ባለስቲክ ሚሳኤሎችን መተኮሷን የጃፓን የመከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል