የምድብ 1 ሀገራት ስኮትላንድና ሀንጋሪ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በስቱትጋርት አሬና ስታድየም ጨዋታ የሚያደርጉ ይሆናል።
ሀገራቱ ከዚህ ቀደም 9 ጊዜ የተገናኙ ሲሆን፤ 3 ጊዜ ስኮትላንድ እና 4 ጊዜ ደግሞ ሀንጋሪ አሸንፋለች። በቀሪዎቹ 2 ጨዋታዎች ሀገራቱ አቻ ተለያይተዋል።
በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ ስኮትላንድ 1 ነጥብ ሲኖራት፤ ሀንጋሪ ምንም ዓይነት ነጥብ የላትም።
በተመሳሳይ፥ በምድብ 1 ጨዋታ ምሽት 4 ሰዓት ላይ አዘጋጇ አገር ጀርመን ከስዊዘርላንድ ጋር በዶቼ ባንክ ፓርክ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
የጀርመኑ አሰልጣኝ ጁሊያን ናጌልስማን “ስዊዘርላንዶች በጣም ጥሩ ተጋጣሚዎች ናቸው፣ በግለሰብ ደረጃ የተጫዋች ጥራትን በተመለከተ ስዊዘርላንድን ጠንካራ ተጋጣሚ አድርጌ እቆጥራለሁ፤ ሶስተኛውን የምድብ ጨዋታም ማሸነፍ እንፈልጋለን” ብለዋል።
የስዊዘርላንድ አሰልጣኝ ሙራት ያኪን በበኩላቸው፥ “በጉጉት የምንጠብቀው አጓጊ ጨዋታ ነው፤ በእኔ እና በጀርመን አሰልጣኝ ጁሊያን መካከል ያለውን የታክቲክ አጠቃቀም የምናይበት ይሆናል” ብለዋል።
አስቀድማ ማለፏን ያረጋገጠችው ጀርመን በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ 6 ነጥብ ሲኖራት፤ በአንፃሩ ስዊዘርላንድ 4 ነጥብ አላት።
የዛሬው የምድብ ማጣሪያ ጀርመንን በመከተል ወደ ጥሎ ማለፍ የሚያልፈው ሀገር የሚለይበት ወሳኝ ጨዋታ ነው።
EBC
More Stories
የአለም የማራቶን ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበችው ሩት ቼፕንጌቲች የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የክብር እንግዳ ትሆናለች
ኢትዮጵያና ዑጋንዳ ዛሬ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ
በፕሪሚየር ሊጉ ሊግ ማንቸስተር ዩናይትድ እና አስቶንቪላ አቻ ተለያዩ