January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የኢትዮጵያ አየር መንገደ በዓለም ላይ ምርጡ የአየር መንገድ ነው – አምባሳደር ቲቦር ናዥ

የኢትዮጵያ አየር መንገደ በዓለም ላይ ምርጡ የአየር መንገድ ነው ሲሉ የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ አምባሳደር ቲቦር ናዥ ገለፁ፡፡

አምባሳደር ቲቦር ናዥ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልእክት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ በአቪዬሽን ዩኒቨርሲቲው ላስመረቃቸው 800 ተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።

አምባሳደሩ በመልእክታቸውም፤ የኢትዮጵያ አየር መንገደን ብዙ ጊዜ መጎብኘታቸውን ጠቅሰው፤ በነበራቸው ተሞክሮም የአየር መንገዱ የሙያ ልህቀት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።

ለእኔ የኢትዮጵያ አየር መንገደ በዓለም ላይ ምርጡ የአየር መንገድ ነው ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡

EBC