January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ድጋሚ ምርጫ ጊዜያዊ ውጤቶች ይፋ እየተደረጉ ነው

 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተካሄደው ድጋሚ ምርጫ ድምጽ የተሰጠባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ ውጤቶችን ይፋ እያደረጉ ነው።

በክልሉ ምሥራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ እና በማረቆ ልዩ ወረዳ 6ኛው ሀገራዊ የድጋሚ ምርጫ ላይ ዜጎች በትናንትናው ዕለት ድምጻቸውን መስጠታቸው ይታወሳል፡፡

በምርጫው ሒደት ሲሳተፉ የነበሩ መራጮችም በዛሬው ዕለት የተለጠፈውን ጊዜያዊ ውጤት እየተመለከቱ ይገኛሉ።

የድጋሚ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ሒደቱ በአካባቢዎቹ በሚገኙ በ169 የምርጫ ጣቢያዎች መከናወኑ ይታወቃል።

FBC