January 22, 2025

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

በደቡብ ራድዮና ቴለቪዥን ድርጅት የማሻ ቅርንጫፍ ጣቢያ የ2016 ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በማሻ ከተማ ተካሂዷል።

የደቡብ ሬድዮና ቴለቪዥን ድርጅት 11ኛ ቅርንጫፍ ሆኖ በቅርቡ የተደራጀው የማሻ ቅርንጫፍ ጣቢያ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከሚገኙት የሚዲያ ተቋማት አንዱ ስሆን ቅርንጫፍ ጣቢያው የተቋቋመው በቅርቡ ቢሆንም በአድማጩና ተከታዩ ዘንድ የተሻለ ተቀባይነት በማግኘት በክልሉ ካሉት ሚዲያ ተቋማት ጋር ተወዳዳሪ ከመሆን ባለፈ ተመራጭ ለመሆን ብዙ ሥራዎችን በማከናወን ለይ እንደሚገኝ ተጠቁሞዋል።የተቋሙን የእስካሁኑን አጠቃላይ እንቅስቃሴ በአፈጻጸም ሪፖርት በጣቢያው ዕቅድ ዝግጅት ለውጥ ግምገማ አስተባባሪ በአቶ አስረስ በቀሌ የቀረበ ስሆን በሰነዱ መነሻ ሰፊ ውይይትና ምክክር ተደርጎዋል።ተሳታፊዎች በአስተያየታቸው ተቋሙ ከተቋቋመበት አጭር ጊዜ ውስጥ ለዞኑና አጎራባች አካበቢዎች የመረጃ ተደራሽ እየሆነ ያለ ሚድያ ነው ብለዋል።የማሻ ኤፍ ኤም 103.8 ስራ ከጀመረ በኃላ ህብረተሰቡ ሚዲያውን በመጠቀም የተለያዩ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በሬዲዮ እያቀረበና ድምፅ በመሆን ምላሽ እዪስገኘ ይገኛል ነው ያሉት።ጀማሪ ሚዲያ በመሆኑ የባለድርሻ አካላት ድጋፍና ክትትል በበቅ ሁኔታ ልደገፍ ይገባል ስሉ ጠቁመዋል።በዞኑ በሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች የተደራሽነት ያለመሆኑን ችግሮች በመኖራቸው መደመጥ የሚችልበት ሁኔታ እንድመቻች ጠይቀዋል።በተለይ የተቋሙ ሰራተኞች ለሚዲያው የሚያስፈልግ ቁሳቁስ ባልተሟለበት ለነዋሪዎች መረጃ ተደራሽ እንድሆን እየሰሩ በመሆናቸው ልመሰገኑ ይገባል ስሉ ተናግረዋል።በደቡብ ሬድዮና ቴለቪዥን ድርጅት ምክትል ስራ አስኪያጅና የይዘት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ታደሰ ጋረፎ ተቋሙ በአጭር ጊዜ ባልተሟላ ቁሳቁስ ብዙ ስራዎችን መስራቱን እና የታዩ ክፍተቶችን ወደፍት የሚያስፈልገውን መሳሪያዎችን በሟሟላት እንደሚሰራ ጠቁመዋል።በደቡብ ሬድዮና ቴለቪዥን ድርጅት ማሻ ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ታምሩ ጉዱ በበኩላቸው ተቋሙን በዞኑ ለማቋቋም ብዙ ፈተናዎች መተላለፋቸውን አንስተው ዕውቀትን ባማከለ የሰው ሀይል መደራጀቱን አብራርተዋል።በሶስት መንገድ ለሕብረተሰቡ መረጃ ተደራሽ እየሆነ እንዳለ በመግለፅ ተቋሙ በበለጠ ለማዘመንና ተወዳዳሪ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እየተሰራ እንዳለ ጠቁመዋል።አሁን ላይ ከአካባቢው አልፎ አዲስ አበባ ላይ በጥራት እየተደመጠና በቅርበት በጥራት በማይደመጡ አካባቢዎች ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመፍታት እየተሰራ ነው ብለዋል።የሸካ ዞን ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች መመሪያ ሀላፊ ወ/ሮ ትዕግስት ከበደ በበኩላቸው ለበርካታ ዓመታት የህዝብ ጥያቄ የነበረው የሚዲያ ተደራሽነት ጉዳይ ምላሽ በማግኘት የመረጃ ተደራሽ መሆን ችለዋል በማለት የተደራሽነት ክፍተት ለመሙላት መደገፍ ባለብን መንገድ እንደ ዞን እንደግፋለን ያሉ ስሆን ለሚዲያው የሚያስፈለገውን ቁሳቁስ ለሟሟላትና ለሚዲያ አስፈላጊውን መረጃ ለማቅረብ ትብብር ይደረጋል ብለዋል።