የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በሰው ኃይል ልማት በተለይም ብቁ የሰራዊቱን አመራሮች ለማፍራት ከለውጡ ወዲህ ውጤታማ ስራ መከናወኑን ገለጹ።የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን ከኢፌዴሪ አየር ኃይል የተውጣጡ 24 የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች በሠርተፊኬት አስመርቋል።ከፍተኛ አመራሮቹ በሀገራዊ፣ አካባቢያዊ እና ዓለም አቀፋዊ እንዲሁም ጦርነት ጠቅላላ ንድፈ ሀሳቦችን ጨምሮ በመሰል ተዛማጅ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መሰልጠናቸው ተገልጿል።በስልጠናው ማጠቃለያ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ፤ አየር ኃይሉ በሰው ኃይል ልማት በተለይም ብቁ የሰራዊቱን አመራሮች ለማፍራት ከለውጡ ወዲህ ውጤታማ ስራ ማከናወኑን ገልጸዋል።ተቋሙ በሁሉም መስክ ላስመዘገበው ስኬት በዋነኝነት የቁርጠኛ አመራር ሚና ወሳኝ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።የመከላከያ ዋር ኮሌጅ በወታደራዊ ሳይንስ እና ጥበብ የተካኑ የወደፊቱን የጦር መሪዎችን ለማፍራት የሚያከናውነው ስራ እጅግ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው፤ አየር ኃይሉም ከኮሌጁ ጋር ተባብሮ የመስራት ግንኙነቱን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።የመከላከያ ዋር ኮሌጅ ዋና አዛዥ ብርጋዲዬር ጄኔራል ቡልቲ ታደሰ በበኩላቸው፤ ተቋማቱ ለአንድ አይነት አላማ በጋራ የተሰለፉ መሆናቸውን አንስተዋል።በማስተማር፣ ሀሳብ በመስጠት እና ሁኔታዎችን በማመቻቸትም ጭምር ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን መግለጻቸውን የመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመልክቷል።በአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ የተሰጠው ስልጠና አመራሮቹ ከስራ ቦታቸው ሳይርቁ በንድፈ ሀሳብና በተግባር ልምምድ የተደገፈ ውጤታማ ስልጠና መሆኑን የመከላከያ ዋር ኮሌጅ አካዳሚክ ዲን ኮሎኔል ጥላሁን ታደሰ ገልጸዋል።
FBC
More Stories
የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ከነገ በስቲያ ያበቃል
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋለውን ዘርፈብዙ ችግር ለመቅረፍ የትራንስፖርት ማህበራት ቅንጅትና መናበብ ወሳኝ መሆኑ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።