July 4, 2024

Masha Fm Woreda to World

Woreda to World

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) መድኃኒቶችን በራስ ዐቅም ማምረት ለነገ የሚተው አለመሆኑን አስገነዘቡ

ከ120 ሚሊየን በላይ ሕዝብ ላላት ኢትዮጵያ መድኃኒቶችን በራስ ዐቅም ማምረት ለነገ የሚተው ጉዳይ አይደለም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገር ውስጥ የሕክምና ግብዓት ምርትና ኢኖቬሽን ዐውደ-ርዕይን መርቀው ከፍተዋል፡፡ይህን ተከትሎም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ የሀገር ውስጥ የሕክምና ግብዓቶችንና እና መድኃኒቶችን ለማምረት የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ከማድረግ ጀምሮ ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸዋል።እንዲሁም መድኃኒት እና የሕክምና ግብዓቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን አስቻይ ሁኔታዎች መዘጋጀታቸውን በዐውደ-ርዕዩ ላይ ባደረጉት ንግግር አስታውቀዋል፡፡”ጤናችን በምርታችን” በሚል መሪ ሐሳብ የተከፈተውን ዐውደ-ርዕይ የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ መድኃኒት አምራቾች ማኅበር በጋራ አዘጋጅተውታል፡፡ለሥድስት ቀናት ለሕዝብ ክፍት ሆኖ በሚቆየው ዐውደ-ርዕይ ላይ÷ ከ110 በላይ የዘርፉ አምራቾች እንደሚሳተፉበት ተገልጿል፡፡

FBC